EDP
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow

Subscribe to our Newsletter







ኢዴፓ በሣምንቱ መጨረሻ በአዲስ አበባና በደሴ ስብሰባዎችን ያካሂዳል E-mail
Thursday, 29 April 2010 07:43
Ethiopia - EDP's Dessie Meeting
የደሴ ስብሰባ
Ethiopia - EDP's Hawassa Public Meeting
የሀዋሳ ስብሰባ
(pdf) የምርጫው ዕለት እየተቃረበ በመምጣቱ የምረጡኝ ዘመቻውን አጠናክሮ የቀጠለው የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በዚህ ሳምንት መጨረሻ በሁለት ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባዎችን ለማካሄድ ማቀዱን ከኢዴፓ የውጭ ግንኙነት የተላከልን መረጃ አመለከተ፡፡

ከመረጃ ምንጩ በተላከልን መረጃ መሰረት፣ ዕሑድ ሚያዝያ 24 ቀን 2002 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በውሃ ሃብት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ እንዲሁም በዚሁ ዕለት በደሴ ከተማ በወሎ ባህል አምባ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚካሄዱ ታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ወ/ሮ ሶፍያ ይልማና ዋና ጸሐፊውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራር አባላት የሚገኙ ሲሆን፣ በደሴው ህዝባዊ ሰብሰባ ላይ ደግሞ አቶ ልደቱ አያሌው፣ አቶ አብዱራህማን አህመዲን እና አቶ ዳንኤል ኃ/ማርያም እንደሚገኙ የዜና ምንጩ ጨምሮ ገልጿል፡፡
ቅዳሜ ዕለት በኦሮሚያ በአዳማ (ናዝሬት) እና በሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን ከተሞች ተጨማሪ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ለማካሄድ ዕቅድ ተይዞ እንደነበር የዜና ምንጩ ጠቅሶ፣ ይሁን እንጂ በሁለቱ ከተሞች ያሉት ዋና ዋና አዳራሾች ቀድመው የተያዙ በመሆኑ ስብሰባውን ለማካሄድ እንዳልተቻለና ወደሚቀጥለው ሳምንት እንደተላለፈ አስታውቋል፡፡
 

Ethiopian Democratic Party - Election 2010 Campaign
(Photo slideshow)

edpLalibelacustom

ከሌሎች የዜና ምንጮች