EDP
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow
  • An Image Slideshow

Subscribe to our Newsletter







ኢዴፓ በአዲስ አበባ 3 ስብሰባዎችን አካሄደ፤ በጐዳናዎች ለአራት ቀናት የማጠቃለያ ቅስቀሳ ማድረግ ጀመረ E-mail
Monday, 17 May 2010 13:41
Ethiopian Democratic Party- Lalibela Public Rally
በላሊበላ ከተማ የተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በሳምንቱ ማጠናቀቂያ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ሦስት ህዝባዊ ስብሰባዎችን ማድረጉን ከስፍራው የተላከልን መረጃ አመለከተ፡፡ በዚሁ መሰረት፣ ቅዳሜ ዕለት ከሰዓት በኋላ በመብራት ኃይል አዳራሽና በካዛንቺስ በወረዳ 15 ቀበሌ 17/18 አዳራሽ፤ እንዲሁም ዕሁድ ዕለት በቀድሞው መነን በአሁኑ የካቲት 12 የመሰናዶ ት/ቤት ህዝባዊ ስብሰባዎችን በማድረግ የምርጫ ማንፌስቶውን ማስተዋወቁን የዜና ምንጩ ዘግቧል፡፡

በመብራት ኃይል አዳራሽ የተካሄደውን ስብሰባ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ልደቱ አያሌው የመሩት ሲሆን፣ ዕሁድ ዕለት በየካቲት 12 ት/ቤት የተካሄደው ስብሰባ ደግሞ በዋና ፀሐፊው በአቶ ሙሼ ሰሙ እንደተመራ ከስፍራው የደረሰን ዜና ጨምሮ ገልጿል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ፣ ኢዴፓ በአዲስ አበባ ከተማ ጐዳናዎች ለተከታታይ አራት ቀናት የመኪና ላይ ቅስቀሳ እንደሚያደርግ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ነፃነት ደመላሽ አስታወቁ፡፡

አቶ ነፃነት እንደገለፁት ከሆነ ከዛሬ ሰኞ ግንቦት 9 ቀን ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳው እስከሚጠናቀቅበት ሀሙስ ዕለት ድረስ በአምስት ተሽከርካሪዎች የታጀበ የጐዳና ላይ ቅስቀሳ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡
 

Ethiopian Democratic Party - Election 2010 Campaign
(Photo slideshow)

edpLalibelacustom

ከሌሎች የዜና ምንጮች