ልዩ ዐቃቤ ሕግ የመጨረሻ ሪፖርቱን ሲያቀርብ ኢዴፓ “የነጭ ሽብርን” ጉዳይ አነሳ
የአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘውዳዊ አገዛዝ ከተገረሰሰ በኋላ እስከ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር የነበረው የደርግ ወታደራዊ ሥርዓት ባለስልጣናት የፈጸሟቸውን “የቀይ ሽብር” ወንጀሎች እንዲያጣራና ለፍርድ እንዲያቀርብ ኃላፊነት ተሰጥቶት በ1984 ዓ.ም በኢህአዴግ የሽግግር መንግስት ዘመን ተቋቁሞ የነበረው የልዩ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ሥራውን አጠናቆ የመጨረሻ ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ።
Read more...
12 የክርክር አጀንዳዎች ተመረጡ፤ ክርክሩ የካቲት 5 ይጀምራል ተባለ
ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በኢህአዴግ መካከል የሚካሄደው ክርክርና የምረጡኝ ዘመቻ የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም እንደሚጀምር ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ።
Read more...
የኢዴፓ አጀንዳ በፓርላማ እንዳይቀርብ ኢህአዴግና ህብረት ተቃወሙከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ በመጣው የነዳጅ ዋጋና ከዚሁም ጋር ተያይዞ እየናረ በመጣው የኑሮ ውድነት ዙሪያ ፓርላማው “በተቀዋሚዎች ቀን” እንዲመክርበት ኢዴፓ አጀንዳ ማቅረቡ ይታወሳል። ይኸው አጀንዳ በምክር ቤቱ የአሰራር ደንብ መሰረት በጥር ወር የመጨረሻ ሳምንት ማክሰኞ በሚካሄደው የም/ቤቱ መደበኛ ስብሰባ እንደሚቀርብ ቀደም ሲል ቅንጅት ያቀረበው አጀንዳ በታህሳስ ወር እንዲቀርብ በተወሰነበት ወቅት ስምምነት የተደረሰበት ቢሆንም፤ ኢህአዴግና ህብረት ባቀረቡት ተቃውሞ የኢዴፓ አጀንዳ እንዳይቀርብ መደረጉን በፓርላማ የኢዴፓ ተጠሪ የሆኑት አቶ አብዱራህማን አህመዲን አስታውቀዋል። የኢዴፓ አመራር አባላት በተለያዩ የምርጫ ክልሎች በዕጩነት እየተመዘገቡ ነው፤ አቶ ልደቱ ዛሬ ተመዘገቡየኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በግንቦት ወር 2002 ዓ.ም በሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ፣ ከሀገሪቱ የቆዳ ስፋት ሰባ አምስት በመቶ በሚሆነው አካባቢ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ለማቅረብ ካለፈው ሐምሌ ወር 2001 ዓ.ም ጀምሮ ዝግጅት ሲያደርግና የማደራጀት ስራ ሲያከናውን ከርሞ ዕጩ ማስመዝገብ መጀመሩን ከፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ያገኘነው መረጃ አመለከተ። "አደይ አበባ" የኢዴፓ የምርጫ ምልክት ሆኖ ተመረጠየኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ቀደም ሲል በተካሄዱ ምርጫዎች ሲጠቀምበት የነበረውን የሁለት ጣቶችን ምስል የያዘ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እንዲለውጥ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ለውጥ ማድረጉን ከፓርቲው ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመለከተ። |
|
|
| Page 3 of 12 |








