በሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን የአፈጻጸም ሂደት በያዘው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በኩል በተደረገው ጥሪ መሰረት የኢዴፓ ተወካዮች በቦርዱ ጽ/ቤት በመገኘት አስተያየት ማቅረባቸውን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ደረጀ ደበበ አስታወቁ፡፡
የዘንድሮው ምርጫ ግንቦት 15 ቀን ይካሄዳል ተባለበሀገሪቱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን የአፈጻጸም ሂደት በያዘው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በኩል በተደረገው ጥሪ መሰረት የኢዴፓ ተወካዮች በቦርዱ ጽ/ቤት በመገኘት አስተያየት ማቅረባቸውን የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ደረጀ ደበበ አስታወቁ፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በኢህአዴግ መካከል የተጀመረው ድርድር የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀየኢዴፓ ማዕከላዊ ምክር ቤት ውሳኔዎችን አሳለፈየኢዴፓ ማዕከላዊ ምክር ቤት ሁለት ተከታታይ ስብሰባዎችን በማካሄድ በመጪው ግንቦት ወር 2002 ዓ.ም በሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊና ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎች ማሳለፉን ከፓርቲው የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ አመለከተ፡፡ ኢዴፓ በኢህአዴግና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል በሚካሄደው ድርድር በመሳተፍ ላይ መሆኑ ታወቀየኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በኢህአዴግና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል በሚካሄደው ድርድር በአራት ተወካዮቹ አማካይነት በመሳተፍ ላይ መሆኑን ከፓርቲው የውጭ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ አመለከተ፡፡ ኢዴፓን ወክለው በዚህ ድርድር ላይ የሚሳተፉት አቶ ሙሼ ሰሙ፣ አቶ አብዱራህማን አህመዲን፣ አቶ መስፍን መንግስቱ እና አቶ ደረጀ ደበበ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ኢዴፓ በ2001 ዓ.ም ያከናወናቸውን ተግባራት ለመገናኛ ብዙሃን ገለጸየኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የፖለቲካ ፓርቲዎች በ2001 ዓ.ም ያከናወኗቸውን ተግባራት እንዲገልጹ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት፣ በኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በኩል በዓመቱ የተከናወኑ ተግባራትን የሚገልጽ ሪፖርት ተዘጋጅቶ መላኩን የፓርቲው ጽ/ቤት አስታወቀ። |
|
|
| Page 7 of 12 |








