ለፓርቲያችን ላለዎት መልካም ምኞትና ለሚያደርጉልን እገዛ ከልብ ነው የምናመሰግነው። ኢዴፓ የጠራ አማራጭ ፕሮግራም ያለው፤ በጥላቻና በኩርፊያ ሳይሆን በመወያየትና አብሮ በመስራት ፖለቲካ የፀና እምነት ያለው፤ ከሌሎችም ሆነ ከራሱ ጥፋትና ስህተት የመማር ድፍረት ያለው፤ በተጨባጭ ምክንያት የሚደግፍና የሚቃወም፤ ከይሉኝታና ከእወደድ ባይነት የፖለቲካ አመለካከት የፀዳ አቋም የሚያራምድ፤ ስለትናንቱ ሳይሆን ስለዛሬዋና ስለወደፊትዋ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ የበለጠ የሚጨነቅ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፓርቲ ነው። ኢዴፓ የመንግሥት ለውጥ ብቻ ሳይሆን በአገራችን ተስማሚና ዘላቂ የፖለቲካ ሥርዓትን ለማስፈን የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ ድርጅት ነው። በረዥሙ ያለመው ግብ እስከሚደርስ ድረስ በየእርከኑ ያሉበትን መሰናክሎች በሃቅ፡ በጽናትና በጥበብ እየተጋፈጠ በአሸናፊነት ለማለፍ እስካሁን ያደረጋቸው ጥረቶችና ውጤቶች የሚያበረታቱ ናቸው። በተለይም ካለፈው ምርጫ በኋላ የድርጅቱን ድጋፍ ለማመናመን የተደረገበትን መጠነ-ሠፊ ዘመቻ ተቋቁሞ አንገቱን ቀና አድርጎ ለመዝለቅ መቻሉ ብሩሕ ተስፋውን አለምልሞለታል። ኢዴፓ ትግሉ ጠንከርና ከረር ሲል የቆመላቸውን ዓላማዎችና መርሖዎች ትቶ ዘወር የሚል አይደለም። መከፈል ያለበትን መስዋእትነት ሁሉ ከፍለው ሃገራቸውን ወደተሻለ ዘመን ለመውሰድ ቆርጠው የተሰለፉ አባላት ያሉበት ፓርቲ ነው። ይኽ የአገር ተስፋ የሆነ ድርጅት ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ለኢትዮጵያ ቅን አሳቢ የሆኑ ዜጎች ሁሉ እገዛ እንዲያደርጉለት ይፈልጋል። ስለሆነም አቅመዎ የፈቀደውን ያህል ቀጥሎ ባሉት የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች እርዳታዎን እንዲለግሱን በአክብሮት እንጠይቃለን።
To all members, supporters and sympathizers of the Ethiopian Democratic Party (EDP):
Our party relies on the generous donations from our members and supporters to ensure its financial footing
To support the party financially please donate straight to our bank account here:
EDP
Abyssinia Bank,
Filwuha Branch,
A/C No. 145,
Addis Ababa
Ethiopia
or alternatively use the following account number:
BARCLAYS BANK PLC
EDP Trust Fund
Account Number: 80121487
Sort Code: 207174



Donate








